በአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ሞሪታንያዊ አጥቂ የግሉ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካደረጋቸው ስድስት መርሃግብሮች አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ሁለት ድል ፣ ሁለት አቻ እና ሁለት ሽንፈት በማስተናገድ በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ላይ በስምንት ነጥቦች ተቀምጠው የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በነፃ ዝውውር የሞሪታኒያ ዜግነት ያለውን አጥቂ ወደ ቡድናቸው በዛሬው ዕለት ቀላቅለዋል።
ሲዲ ማታላ የተባለው አጥቂው በሀገሩ ክለቦች ቲጂክጃ እና ቴቭራግ በመቀጠል በሳዊዲ አረቢያ በሁለተኛው የሊግ ዕርከን ተሳታፊ በሆኑት አል-ኢንቲሳር ካሳለፈ በኋላ ሊቢያዎቹ አል-ሳዳቅ እና አል-ኢንቲሳር ግልጋሎት ከሰጠ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው የሀገራችን ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል ፤ በነፃ ዝውውር ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋቹ የኢትዮጵያ ቡናን የውጪ ተጫዋቾቾቹን ቁጥር አምስት አድርሷል።