አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስለሚከተሉት አጨዋወት ምን አሉ?

👉 “ በዓላማ ኳስን የሚጫወት ፤ የሚቀማውን ኳስ በመቀማት በሽግግር የሚጫወት ቡድን እየሠራን ነው…

ጊዜያዊው የብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የጨዋታ መንገዳቸው ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ይሄንን ብለዋል።

ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ከታንዛኒያ እና
ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር በኪሻንሳ የኮንጎ ዲሪ. ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታዎች ዙርያ እና  መሰል ጉዳዮችን አስመልክቶ ዋና አሰልጣኙ መሳይ ተፈሪ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል። አሰልጣኙ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ብሔራዊ ቡድኑን ሲያሰለጥኑ ስለሚከተሉት የጨዋታ መንገድ ተጠይቀው ሲመልሱ

“በዓላማ ኳስን የሚጫወት የሚቀማውን ኳስ በመቀማት በሽግግር የሚጫወት ቡድን እየሠራን ነው። ኳስ በዓላማ የሚጫወት ኳሱን ስናጣ በፍጥነት በመቀማት በሽግግር ወደ ባላጋራ ቡድን መድረስን ሲሆን ይህ ከእኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ያስፈልጋል ብዬ እስባለሁ። ይህ ሲባል ባላጋራ ቡድንን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ኳስን ስንቆጣጠር ወደ ፊት የማያድግ ነገር እናያለን ፤ ትዕግስት ይፈልጋል። ክፍት ሲሆን ግን በፍጥነት ማጥቃት ይፈልጋል። ሲዘጋ ደግሞ እስኪከፈት ድረስ ትዕግስት አድርገን ማጥቃት አለብን። እነዛ ኳሶች ከእግሮቻችን ሲወጡ ጋፖቻችንን ጠብቀን ኳሶችን ቶሎ መንጠቅ ያለበትን ቡድን ለመገንባት ነው እየሠራን ያለነው።”