ሦስት ተጫዋቾች ከዋልያዎቹ ጋር አይጓዙም

ነገ ወደ ኪንሻሳ የሚያቀኑት የመጨረሻ 20 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ተለይተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ኮንጎ ዲ/ሪ ከማምራቱ አስቀድሞ የመጨረሻ የሀገር ቤት ልምምዱን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያከናወነ ሲሆን ከሰዓት በኋላም የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እና የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አስነብበናችሁ ነበር።


አሁን በተገኘው መረጃ ደግሞ 20 ተጫዋቾችን ጨምሮ 27 የልዑክ ቡድን አባላት ያካተተው ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ረፋድ 4 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ኮንጎ ዲ/ሪ የሚያመራ ይሆናል።

በዚህም ምክንያት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ 20 ተጫዋቾች ማለትም

ግብ ጠባቂዎች

ሰዒድ ሀብታሙ
ፍሬው ጌታሁን

ተከላካዮች

ብርሃኑ በቀለ
አሥራት ቱንጆ
ያሬድ ባየህ
ፍሬዘር ካሣ
ራምኬል ጀምስ
አማኑኤል ተርፋ
ዳዊት ማሞ
ያሬድ ካሣዬ

አማካዮች

ሬድዋን ናስር
አብነት ደምሴ
አብዱልከሪም ወርቁ
አማኑኤል ዮሐንስ
በረከት ወልዴ

አጥቂዎች

ቸርነት ጉግሳ
በረከት ደስታ
መሐመድኑር ናስር
አንተነህ ተፈራ
አማኑኤል ኤርቦ

ወደ ኪንሳሻ የሚያመሩ 20 ተጫዋቾች መሆናቸው ሲረጋገጥ

አብዩ ካሳዬ
ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን
ቢኒያም አይተን

ደግሞ ከብሔራዊ ቡድኑ የተቀነሱ ሦስት ተጫዋቾች ሆነዋል።