ከሀገራት ውድድር መልስ በተደረገው የሊጉ ቀዳሚ ጨዋታ በአርባምንጭ ከተማ 2ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ በረከት ደሙ – አርባምንጭ ከተማ
“ጨዋታው ጥሩ ነው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴውም ጥሩ ነበር ፣ ግን ከሀያ ቀን አካባቢ ዕረፍት ነው የመጣነው የጨዋታ ዝግጁነት ችግር ሊኖርብን እንደሚችል ይጠበቃል። ተጋጣሚያችንም አሰልጣኝ ቀይሮ በአዲስ ተነሳሽነት ነው የመጣው ምንም ነጥብ አልነበራቸውም እና ጥሩ አጀማመር ለማድረግ ወሳኝ ሰዓት ስለመጡ እነርሱን በደንብ ተቆጣጥሮ ወደ እኛ ማምጣት ቀላል አልነበረም እና ልጆቻችን ተረጋግተው ተገቢውን እንቅስቃሴ አድርገው ነው ውጤቱን ያመጡት”።
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ
“ጨዋታው መጥፎ የሚባል አይደለም ፣ ማስተካከል የሚገቡን ነገሮች አሉ በመከላከል አደረጃጀት ላይ ትንሽ የሚቀረን ነገር አለ እርሱን ማስተካከል ነው። አሁን የእኛ ቡድን ውጤት ነው ማሸነፍ ነው የሚፈልገው ማሸነፍ ስትፈልግ ደግሞ የመከላከል አደረጃጀትህን መፈተሽ ያስፈልጋል እና በጥቃቅን ስህተቶች ነው የገቡት ግን ኳሱን ለመቆጣጠር እንሞክራለን ኳስ መጫወት ብቻ ውጤታማ አያደርግም ታክቲካሊ መስራት ያለብን ነገሮች አሉ።”