የዕለቱ ቀዳሚ መርሐግብር ያለ ግብ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው – ሲዳማ ቡና
“በሁለታችንም በኩል የነበረው የማሸነፍ ፍላጎት ጥሩ ነበር። ከባህር ዳር ጨዋታ በኋላ 6 ተጫዋቾች ወደ ሆስፒታል ነበር የሄዱት ደንጊ በሚባል በሽታ እና የነበረው ዕረፍት ጠቅሞናል። በአቻው ደስተኛ አይደለሁም ግን አልተበሳጨሁም።”
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
“በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን መቆጣጠር ችለናል ማሸነፍ ይገባን ነበር ፤ አንድ ነጥብ ያንሰናል። ተጫዋቾቼ ቀና ብለው መሄድ ይገባቸዋል ምክንያቱም ጎል ከማስቆጠር ውጪ ሁሉንም ማድረግ ችለዋል።”