ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ከተጋሩበት የዕለቱ የመጀመርያ ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው ቀርቧል።
አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ
“ጥሩ ጨዋታ ነበር። ከዕረፍት በፊት እና በኋላ የነበረን እንቅስቃሴ የተለያየ ነበር። ከዕረፍት በፊት የተሻልን ነበርን፤ ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም ሲገባን አንዷን ብቻ አስቆጥረን መቆየታችን ከዕረፍት በኋላ ደግሞ እነሱ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገው ነጥብ ተጋርተን መውጣት ችለናል። ጥሩ እንቅስቃሴ ነው።”
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
“ያለፉትን ጨዋታዎች ነጥብ መያዝ አልቻልንም፤ ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈናል። ከዛ ስሜት ለመውጣት ቢያንስ ግብ ማስቆጠር ባንችልም ግብ ማስተናገድ እንደሌለብን ተነጋግረን ለዛ የሚሆን ነገር ይዘን ነበር የገባነው፤ ሜዳ ውስጥ ያየነው ነገር ግን እሱን አይደለም። ኳሱን መቆጣጠር አልቻልንም ጥቃቶችንም ማቆም አልቻልንም በዛ ላይ ራሳችን ላይ ግብ አስቆጠርን…”
ሙሉ አስተያየቶችን ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ – LINK