የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሑል ሽረ 0-2 ባህርዳር ከተማ

“…ሁል ጊዜ ያላስተካከልነው ጉዳይ አለ” አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት

“በመጀመሪያው አርባ አምስት ደቂቃ የቸገረን ነገር የለም” አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው

ከዕረፍት መልስ ወንድወሰን በለጠ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ባህርዳር ከተማ ስሑል ሽረን መርታት ከቻለበት ጨዋታ መቋጫ በኋላ ሶከር ኢትዮጵያ ከሁለቱም አሰልጣኞች ጋር ቆይታን አድርጋለች።

አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት – ስሑል ሽረ

“ጨዋታው ጥሩ ነው መቼም ሁል ጊዜ ያላስተካከልነው ጉዳይ አለ ፣ ያገኘናቸውን ዕድሎች መጠቀም አልቻልንም። ባህርዳር ከተማ በኳስ ቁጥጥርም ያገኟቸውን ዕድሎችም በመጠቀም ከእኛ የተሻሉ ነበር። ከዕረፍት በኋላ በነበረው ጨዋታ እኛም ያገኘናቸውን ዕድል ባለመጠቀማችን ሁለት ለባዶ ተሸንፈናል።”

አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው – ባህርዳር ከተማ

“ተጋጣሚያችን ጠንካራው ሽረ ነው ፤ እያንዳንዱ ጨዋታ ፈታኝ ነው። በመጀመሪያው አርባ አምስት ደቂቃ የቸገረን ነገር የለም ጨዋታውን ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረናል በተደጋጋሚ የግብ ዕድሎችን ፈጥረናል ፣ ለማሸነፍ ከነበረ ጉጉት በተለይ ሦስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ የመጨረሻው ንክኪያችን ልክ አልነበረም ፣ መቻኮሎች ይታዩበት ነበር በተለይ አንዳንድ ለማመን የሚያስቸግሩ ኳሶች ነበር ይባክኑ የነበሩት ነገር ግን ሒደቱ በጣም ጥሩ ነበር የነበረው አሁንም የግብ ዕድሎችን ልጆቻችን ለመፍጠር የሚሄዱበት መንገድ ጥሩ ነበር።”

ሙሉውን የአሠልጣኞች አስተያየት ለማዳመጥ ይሄንን ይጫኑ