”በሕይወቴ ለአቻ በፍጹም አስቤ አላውቅም” አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ
”የውጤቱ መስፋት እንቅስቃሴውን ይገልጻል ብዬ አላስብም።” አሰልጣኝ በረከት ደሙ
ጦሩ አዞዎቹን በመርታት መሪነቱን ካጠናከረበት ከምሽቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል
”እኛ በፈለግነው መንገድ ነው ጨዋታው የሄደው ፤ ተጫዋቾች የተሰጣቸውን ነገር በሚገባ ተወጥተዋል ብዬ አስባለሁ። እንኳን መቻልን ያህል ቡድን ይዤ ቀርቶ ከዛም በታች በሆነ ቡድን ለአቻ አልመጣም ፤ በእኛ ቡድን ሁለት ተከታታይ አቻም አይፈቀድም። ግብ የማግባት እንቅስቃሴያችን ተለውጧል አሁንም ይቀረናል ነገር ግን ካለፈው የተሻልን ነን።”
አሰልጣኝ በረከት ደሙ – አርባምንጭ ከተማ
”ጥሩ መንቀሳቀስ ችለናል ፤ ጥቃቅን ግን ወሳኝ ስህተቶችን ሰርተናል። ይሄ ሽንፈት በዚህን ያህል መስፋት ይገባናል ብዬ አላስብም ፤ ከእንቅስቃሴ አንፃር ጥሩ ነው ከውጤት አንፃር ግን ጥሩ አልነበረም። አንዳንድ ከእኛ ውጪ የሆኑ የውሳኔ አሰጣጦች በተወሰነ መልኩ ተጫዋቾቻችንን ስሜታዊ አድርጓቸዋል።”