የአሰልጣኞች አስተያየት| ሲዳማ ቡና 0 – 1 ፋሲል ከነማ

“ፋሲልን የሚመስል ቡድን ለማየት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

“ለዋንጫ የምንጫወት ከሆነ እያንዳንዱን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን” አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው

ፋሲል ከነማ በበረከት ግዛው ብቸኛ ግብ ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ከተመለሰበት ጨዋታ መጠናቀቅን አስከትሎ የሁለቱም ክለብ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
“የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፋችን ትልቁ ነገር ነው። ወደ ማሸነፍ ለመምጣት እጅግ ዘግይተናል። በእያንዳንዱ ጨዋታዎች የተሻሉ ነገሮች ቢኖሩንም በትናንሽ ነገሮች ስንሸነፍ ነበር። ዛሬ ግን ከመጀመርያው ጀምሮ የነበረን ትኩረት፣ ጨዋታውን ለመቆጣጠር የሄድንበት መንገድ እና ብልጫ ለመውሰድ ያደረግነው ጥረት ከፍተኛ ነበር። በዚህ መሰረት ሲዳማ ትልቅ ቡድን ነው፤ ፋሲልን የሚመስል ቡድን ለማየት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ።

ዘላለም ሽፈራው – ሲዳማ ቡና
“ጨዋታውን መጥፎ የሚባል አይደለም። ከውጤት አንፃር መጥፎ ነው ግን ከእነሱ በተሻለ በርካታ አጋጣሚዎች አግኝተናል። የመጨረስ አቅማችን ደካማ ነበር፤ አንድ ስሕተት ሰራን እሱ ደግሞ ተቆጠረብን። መምጣት አለብን፤ ለዋንጫ የምንጫወት ከሆነ እያንዳንዱን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link