”ባለቀ ሰዓት ጎል ማስተናገድ ያሳምማል” አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ
”እኛ ለእያንዳንዱ ጨዋታ ተገቢውን ትኩረት እና ክብር ሰጥተን ነው የምንጫወተው” አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው
ባህር ዳር ከተማ በጭማሪ ደቂቃ ባስቆጠሩት ግብ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ
”አንዱን ለማስጠበቅ ትንሽ ወደኋላ አፈግፍጎ የመጫወቱ መንገድ ያ ነገር ዋጋ ሊያስከፍለን ችሏል። ተከታታይ ጨዋታዎችን ስንሸነፍ የኮንሰንትሬሽን ችግር ነው እንጂ የአቅም ችግር አልነበረም። ካደረግነው ነገር አንፃር ሶስት ነጥብ ይዘን ብንወጣ ይገባን ነበር። ሁለቴ ተከታታይ ከመሸነፍ ሦስት ነጥብ ይዘህ መውጣት ትልቁ ነገር ነበር ያንን ሳናሳካ ስንቀር ደግሞ አንድ ነጥብ ተካፍለን መውጣታችን ቀላል አይደለም።”
አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ
”ከሦስት ቀን በኋላ ያደረግነው ጨዋታ ነው ፣ ተጋጣሚያችን ረጅም ዕረፍት አድርጎ የመጣ ቡድን ነው። ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ በማጥቃት ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ነበር ስናደርግ የነበረው። ውጤቱን ለመቀየር ተጫዋቾቻችን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ የሄዱበት ርቀት እጅግ በጣም የሚያስደስት ነው። ተጫዋቾቻቹችን ሰዓቱ እየገፋ በሄደ ቁጥር ያላቸው ፊትነስ ከፍ ያለ ነው።”