“የእውነት አምላክ ይፍረድ ብቻ ነው የምለው።” አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ
“በመጨረሻ ደቂቃዎች የምናስተናግዳቸው ጎሎች በጣም ያስቆጫሉ።” አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ
ኃይቆቹ በ90+5ኛ ደቂቃ ባስቆጠሩት ግብ ከወላይታ ድቻ ጋር 1-1 ከተለያዩበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኝ ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል።
አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ
“በዛሬው ጨዋታ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገናል ነገር ግን ባለቀ ሰዓት አጥቂውም ሳያስበው ባስቆጠረው ጎል ነጥብ ተጋርተናል። በመጨረሻ ደቂቃዎች የምናስተናግዳቸው ጎሎች በጣም ያስቆጫሉ።”
አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ
“ቡድናችን ከጨዋታ ጨዋታ ትልቅ ለውጥ አለው። ተደጋጋሚ ሽንፈቶች ሲመጡ ጭንቀቶች ይፈጠራሉ። አንዳንዴ ካላለልህ አላለልህም ነው። ሌላውን ነገር ሕዝብ ይፍረድ ከዚህ ውጪ የምናገረው የለም።”