ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያልተለመዱ ሹመቶችን ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ምርጫን ጨምሮ በአራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቁ ታውቋል።
ጉባዔው ኢንጅነር ኃይለኢየሱስ ፍስሐን ፕሬዚዳንት አድርጎ ሲመርጥ ባልተለመደ መልኩ አርቲስት ማስተዋል ወንድወሰን ምክትል ፕሬዚዳንት እና አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ አቃቤ ነዋይ ሆነው ተመርጠዋል።
ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት በሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩ ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ 9 ሥራ አስፈጻሚዎች በጉባዔተኛው የተመረጡ ሲሆን የአርማ ርክክብም ከቀድሞው የሥራ አስፈጻሚዎች አድርገዋል።