የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 0-0 መቐለ 70 እንደርታ

“ዕድል ከቡድኑም ከእኔ ጋርም አይደለም።” አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ

“ጨዋታውን በመጀመሪያው አጋማሽ መጨረስ ይገባን ነበር።” አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ

የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ያለግብ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ

“ምን እንደያዘን ራሱ ግራ እስከሚገባን ነው ፤ ከሚገባው በላይ የግብ ዕድሎችን ፈጥረናል። ዕድል ከቡድንም ከእኔ ጋርም አይደለም። ከውጪ ያለው ነገር ክለቡን ማፍረስ ነው ፤ ያ ጫና ተጫዋቾቹ ላይ አለ። ቡድኑ ከሚገባው በላይ ዋጋ ከፍሏል።”

አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ

“አጀማመራችን የእኛ የተሻለ ነበር ፤ ጨዋታውን በመጀመሪያው አጋማሽ መጨረስ ይገባን ነበር። ከነበረው ሁኔታ አንጻር መጥፎ ባይሆንም አቻ አይገባንም ነበር።”

ሙሉውን አስተያየት ከስር ይመልከቱ 👇🏽