ዐፄዎቹ ቢጫዎችን በማሸነፍ ተከታታይ ድላቸውን ካሳኩበት ከምሽቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን አስተያየት አጋርተዋል።
”ነጥብ በያዝክ ቁጥር ትልቅ የራስ መተማመን ይሰጥሃል ” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
”በአንድ ግዜ ሁሉንም ነገር ማስተካከል አልቻልንም ” አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
”በመከላከሉም በማጥቃቱም ረገድ የተሻለ ነገር ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው። ነጥብ በያዝክ ቁጥር ትልቅ የራስ መተማመን ይሰጥሃል፣ የዛሬ ማሸነፍ ግን ሌላውን ነገር ሴኪውር ያደርግልሃል ማለት አይደለም። ከፊታችን ብዙ ጨዋታዎች አሉ አሁን ላይ የኔ ቡድን ጥሩ ነው ማለት መቸኮል ነው።”
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
”ሜዳ ላይ የነበረን እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ ነው፣ ተጭነን ለመጫወት ሞክረናል። ቡድኑ ላይ ትንሽ ፕሮግረስ ይታያል ግን ወደ ውጤት መቀየር ይጠበቅብናል ፣ በአንድ ግዜ ሁሉን ነገር ማስተካከል አልቻልንም። የተጎዱ ተጫዋቾች ሲደርሱ ደግሞ የተሻለ ነገር እናደርጋለን።”
ሙሉውን አስተያየት ከስር ይመልከቱ 👇🏽