አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ ስለ አዲሱ ሹመቷ ዕውቅና እንደሌላት አሳወቀች

በትናንትናው ዕለት የአ.አ እግርኳስ ፌዴሬሽን አቃቤ ነዋይ ሆና የተመረጠችው አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ ስለ ሹመቱ ዕውቅና እንደሌላት በግል ማኅበራዊ ገጿ አሳወቀች።

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት አካሂዶ ኢንጅነር ኃይለኢየሱስ ፍስሐን ፕሬዚዳንት አድርጎ ሲመርጥ አርቲስት ማስተዋል ወንድወሰን ምክትል ፕሬዚዳንት እና አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ አቃቤ ነዋይ ሆነው መመረጣቸውን በይፋ ማሳወቁ የሚታወስ ነው።

አቃቤ ነዋይ ሆና የተመረጠችው አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ ግን በግል ማኅበራዊ ትስስር ገጿ ተከታዩን አወዛጋቢ ጽሑፍ አስፍራለች።

“በግሌ በፕሮሞሽን፣ መድረክ መምራት እና መሰል ጉዳዮች በሙያዬ እንዳግዝ በስልክ ተጠይቄ ፍቃደኛ ነኝ በሙያዬ አግዛችኋለሁ የሚል የስልክ ምላሽ ሰጥቻለሁ። መረጃ ዎች ላኪልን ስባልም በፍቃደኝነት ልኬያለሁ። ከዚህ ውጭ ግዮን ሆቴል ተካሄደ ስለተባለ ስብሰባ የማውቀው ነገር አልነበረም፣ በቦታውም አልነበርኩም፣ ጥሪም አልደረሰኝም።”

ይህ ጽሑፍ የሚያመላክታቸውን ነገሮች በትኩረት በመከታተል መረጃዎችን በተከታታይ የምናደርስላችሁ ይሆናል።