የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ማጣርያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ዝግጅት ለተጫዋቾች ጥሪ ቀርቧል።
ታኅሣሥ 13 እና 16 ሊቢያ ቤንጋዚ ላይ እንደሚደረግ በሚጠበቀው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ማጣርያ ከሱዳን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ያሉባቸው ዋልያዎቹ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ሲታወቅ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ 23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።
ግብ ጠባቂዎች
ሰዒድ ሀብታሙ – ሀዋሳ ከተማ
ፍሬው ጌታሁን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዐብዩ ካሣዬ – ድሬዳዋ ከተማ
ተከላካዮች
አሥራት ቱንጆ – ድሬዳዋ ከተማ
ብርሃኑ በቀለ – ሲዳማ ቡና
ያሬድ ባየህ – ሲዳማ ቡና
ራምኬል ጀምስ – ኢትዮጵያ ቡና
አማኑኤል ተርፉ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አህመድ ረሺድ – ድሬዳዋ ከተማ
ሬድዋን ሸሪፍ – አዳማ ከተማ
ያሬድ ካሳዬ – ኢትዮጵያ መድን
አብዱልሰላም የሱፍ – ድሬዳዋ ከተማ
አማካዮች
በረከት ወልዴ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አማኑኤል ዮሐንስ – መቻል
አብዱልከሪም ወርቁ – መቻል
ብሩክ ማርቆስ – ሀዲያ ሆሳዕና
በረከት ግዛው – ፋሲል ከነማ
አበባየሁ ሀጂሶ – ሲዳማ ቡና
አጥቂዎች
በረከት ደስታ – መቻል
ቸርነት ጉግሳ – ባህር ዳር ከተማ
አማኑኤል ኤርቦ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ተመስገን ብርሃኑ – ሀዲያ ሆሳዕና
ስንታየሁ መንግሥቱ – አዳማ ከተማ
*ብሔራዊ ቡድኑ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል በመሰባሰብ ሐሙስ ታኅሣሥ 3 ለጨዋታዎቹ የሚያደርገውን ዝግጅት ይጀምራል።