ተክለማርያም ሻንቆ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል

በሀገረ አሜሪካ የሚገኘው የግብ ዘቡ ወደ ስፍራው ስላቀናበት ምክንያት ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከሕዳር ወር መጀመሪያ ጀምሮ ከክለቡ ጋር የማይገኘው ግብ ጠባቂው በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ሲሆን ክለቡ ስብስቡን እንዲቀላቀል ቀነ ገደብ አስቀምጦ ይፋዊ ደብዳቤ ያወጣ መሆኑን ትናንት መዘገባችን ይታወቃል። በጉዳዩ ዙሪያ የተክለማርያምን ምላሽ ይዘን እንደምንመለስ በገለጽነው መሰረት የግብ ዘቡ ወደ አሜሪካ ስለተጓዘበት ምክንያት እንዲህ በማለት ነግሮናል።

“ሕመም አጋጥሞኝ ለተሻለ ሕክምና ነው ወደ አሜሪካ የተጓዝኩት ይህንንም ለክለቡ አሰልጣኝ አባላት እያንዳንዱን የሕክምናዬን ሂደት እያሳወቅኳቸው ነው። ሕመሜ እጅግ ከበድ ያለ ነበር አሁን ቀዶ ጥገናዬን ጨርሼ የተሻለ ጤንነት ላይ ነኝ እገኛለሁ። ወደ ሀገር ቤትም በጥር አጋማሽ ላይ እመጣለሁ። ያለውን ሁኔታ ከክለቡ ጋር የምነጋገር ይሆናል” በማለት ገልጾልናል።