የአሰልጣኞች አስተያየት| ኢትዮጵያ መድን 3 – 1 ስሑል ሽረ

👉 “ይገባናል ብዬ ነው የማስበው”

👉 “አጀማመራችን ጥሩ ነበር ከዕረፍት በኋላ ግን እንደጠበቅነው አይደለም”

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ | ኢትዮጵያ መድን

“ከውጤት አንፃር ጨዋታው ጥሩ ነው ሰፋ ያለ ውጤት ነው፤ ይገባናል ብዬ ነው የማስበው። በምንፈልገው ያህል ባይሆንም ከሜዳው ጋር ተያይዞ ትንሽ መቆራረጦች አሉ ግን ጥሩ ነው”።

ረዳት አሰልጣኝ ተገኘ ዕቁባይ | ስሑል ሽረ

“ጨዋታው ጥሩ ነበር። አጀማመራችን ጥሩ ነበር ከዕረፍት በኋላ ግን እንደጠበቅነው አይደለም። የሜዳውን ችግር አለ ሁለተኛ ደግሞ ተጋጣሚያችን ኢትዮጵያ መድን ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ናቸው ልምድ ያለው ባለ ሞያ ነው ያለው አሰልጣኙ ስለዚ እነሱ ከኛ በተሻለ ተንቀሳቅሰው ስለነበር የተሻለ የጎል ዕድል ፈጥረዋል”።

ሙሉውን ለመመልከት –