የአሰልጣኞች አስተያየት | መቻል 0-1 ሀዲያ ሆሳዕና

ሀዲያ ሆሳዕና ጫላ ተሺታ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ መቻልን ከረቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ ቀኋላ አሰልጣኞቹ ከሶከር ኢትዮ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

”ውጤቱ ከጠበቅነው በላይ ነው” አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ

”ገና ረጅም ጉዞ ነው ምንጓዘውና ተመልሰን መሪነታችንን እንይዛለን” ረዳት አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ

ረዳት አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ – መቻል

”ጨዋታው ከሞላ ጎደል ጥሩ ነው ማለት አይቻልም፤ የጠብቅነው ውጤት አይደለም። የኛን አጨዋወት ትተን ወደእነሱ መግባታችን እራሱ ተፅዕኖ አሳድሮብናል። ገና ረጅም ጉዞ ነው ምንጓዘውና ተመልሰን መሪነታችንን እንይዛለን።”

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና

”የተሻለ ብልጫ እንወስዳለን ብለን አስበን ነው የገባነው። ውጤቱ ከጠብቅነው በላይ ነው ፤ለምን ተጋጣሚያችን ጥሩ ቡድን ነው። ለየትኛውም ቡድን ተዘጋጅተን ነው ምንገባው ጨዋታው ምን መምሰል እንዳለበት ተጫዋቾቼ በሚገባ ተረድተውልኛል ትልቁ ነገር ያ ነው።”

ሙሉውን አስተያየት ለማድመጥ LINK