የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 0-0 ኢትዮጵያ ቡና

“አንድ ነጥብ መጥፎ አይደለም እንደ ተጋጣሚያችን ጥንካሬ” አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ

“ቫር አይቶ ይሻር ምን አይቶ እንደሻረ እግዚአብሄር ይወቀው” አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ

በሁለተኛው አጋማሽ አወዛጋቢ ክስተቶችን አስመልክቶን ያለ ጎል ከተጠናቀቀው የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።

አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና

“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፣ ተዘጋጅን በመጣነው ፕላናችን በሚገባ ተጫዋቾቼ ያላቸውን ነገር ሰጥተዋል። ብዙ የጎል ዕድሎችን ፈጥረዋል የተሻልን ነበርን ብዬ አስባለሁ ግን ሦስተኛው ሜዳ ላይ ውሳኔዎቻችን ስህተት ነበረበት። ነፍቶ ፔናሊቲ ብሏል ቫር አይቶ ይሻር ምን አይቶ እንደሻረ እግዜአብሄር ይወቀው።”

አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ – ድሬዳዋ ከተማ

“በሁለታችንም በኩል ጥሩ ጨዋታ ነበር ፣ አንዳንዴ እንደ ሜዳው ነው የምትሆነው በዚህ ላይ ተጋጣሚያችን ከፍ ብሎ ነበር እየተጫወተ ያለው ፓዚሺኖችን እያየህ ነው የምትጀምረው። አንድ ነጥብ መጥፎ አይደለም እንደ ተጋጣሚያችን ጥንካሬ።”

ሙሉውን አስተያየት ለመስማት