የጋቶች ፓኖም መዳረሻ ክለብ ታውቋል

ከሰሞኑ የኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ወደ ኤዥያ ማቅናቱ በዘገብነው መሠረት አሁን መዳረሻው ክለብ አረጋግጠናል።

ከኢትዮጵያ መድን በአስራ ሁለተኛው ሳምንት ጨዋታው ስሑል ሽረን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ከክለቡ ጋር ያለውን ቆይታ በማጠናቀቅ መልቀቂያቅን የወሰደው ጋቶች ፓኖም ወደ ኡሲያዊቷ ሀገር ኢራቅ ከትናት በስቲያ ማምሻውን መጓዙን ዘግበንላቹሁ ነበር።

የሄደበት ክለብ እና አጠቃላይ የዝውውር ሂደቱን በተመለከተ መረጃዎችን አጠናክረን እንድንመለስ በገለፅነው መሠረት ፊርማውን እንደሚያኖር የሚጠበቀው ክለብ ነውሮዝ ስፖርት ክለብም ሆኗል። ዝውውሩ በቅርብ ግዚያት በይፋ የሚጠናቀቅ ሲሆን ክለቡም ይህን ዝውውር ይፋ ለማድረግ በማህበራዊ ገፁ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አለማ በማድረግ በቅርብ ቀን የሚል ማስታወቂያ መልቀቁን ተመልክተናል።

ነውሮዝ ክለብ በኢራቅ ኩርዲስታን ግዛት ውስጥ የሚገኝ ክለብ ሲሆን መቀመጫውን በሱላይማኒያ ከተማ ያደረገ እና የሚጫወተው በ14500 ተመልካቾችን በሚይዘው የሱላይማኒያ ስታዲየም ነው፡፡ ክለቡ ምስረታውን ያደረገው እኤአ በ1994 ሲያደርግ ከ31 ዓመት በፊት የተቋቋሙ ሁለት ክለቦች ተዋህደው አዲሱን ክለብ የፈጠሩት። ሁለትም ክለቦችም አዝማር እና ካማል ሳሊም በመባል ይታወቃሉ፡፡

በዚሁ ሊግ ቀድሞ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2010 ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የነበረው ኦኪኪ አፎላቢ ለናፍት ሚሳን ለሚባል ክለብ ሲጫወት በ2015 ደግሞ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነው ኢስማኤል አጎዎሮ በናፋት አል ባራዝ ክለብ እየተጫወቱ ይገኛል። በትናትናው ዕለትም የጋቶች አዲስ ክለብ ነውሪዝ በባራዝ ክለብ 2-0 ሲሸነፍ አንዱን ጎል ኢስማኤል ኦሮ አጎዎሮ አስቆጥሮ ነበር።

ነውሮዝ ዓምና በኢራቅ ስታርስ ሊግ ሰባተኛ ሆኖ መጨረሱ ሲታወስ ዘንድሮ 20 ክለቦች በሚሳተፉበት ሊግ በ14 ነጥብ 16ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።