የአሰልጣኞች አስተያየት| ሀድያ ሆሳዕና 1 – 1 ፋሲል ከነማ

ነብሮቹ እና ዐፄዎቹ ነጥብ ከተጋሩበት የዕለቱ የመጀመርያ ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ያደርጉትን ቆይታ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

አሰልጣኝ  ግርማ ታደሰ – ሀድያ ሆሳዕና

“ጨዋታው ጥሩ ነው፤ በመጀመርያው አጋማሽ ተጋጣሚያችን በመቆጣጠር ረገድ በማጥቃቱም ሂደት በመከላከሉም ተደራጅተን የምንከላከልበት መንገድ ጥሩ ነው። የግብ አጋጣሚዎችም አግኝተናል ማስቆጠርም ችለናል ፤ ነገር ግን በሁለተኛው አጋማሽ ያንን ማስቀጠል ተቸግረን ነበር።”

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

“ጥሩ ነው፤ በጣም ጠንካራ ጨዋታ ነው። ሀድያ ያለፉትን ስድስት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት ይዘው ነው የመጡት ጥሩ ሞራል ላይ ናቸው። በጣም ጠጣር ቡድን ነው ‘Aggressive’ ናቸው። ከኳስ ውጭ ጥብቅ ናቸው፤ መከላከሉ ላይም ጠንካራ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ፊት ላይ በርካታ ፈጣን ተጫዋቾች ስላሏቸው ፈጣን ሽግግር ላይም አስቸጋሪ ቡድን ነው። ጠንካራ ጨዋታ እንደሚሆን ጠብቀን ነበር።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link