👉 “ኳሳችንን ከኋላ ማሸራሸር ብቻ ውጤታማ አያደርገንም” – ጊዜያዊ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ
👉 “ጨዋታው በምንፈልገው መንገድ አልሄደልንም” – አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ
የዕለቱ ቀዳሚ መርሐ-ግብር የነበረው የሲዳማ ቡና እና የመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ያለጎል ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞቹ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ጊዜያዊ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ – ሲዳማ ቡና
“ጨዋታውን ተጫውተን ወጥተናል ይሄ ኳሱን የማንሸራሸር ነገር ጥሩ ነው ግን ጎል ካላገባን አስቸጋሪ ነው። እግርኳስ ጨዋታ ጎል ማግባት ማሸነፍ ነው። እዛ ጋር ያለን ነገር የቀዘቀዘ ነው። ኳሳችንን ከኋላ ማሸራሸር ብቻ ውጤታማ አያደርገንም።”
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ- መቐለ 70 እንደርታ
“ጨዋታው በምንፈልገው መንገድ አልሄደልንም። ኳሱን ይዞ ለመጫወት ነበር ሀሳባችን። ግን አንዳንዴ ከቡድኑ የአጨዋወት ሲስተም በምንፈልገው መንገድ ሊሄድልን አልቻለም።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link