የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልዋሎ ዓ/ዩ 0-2 ወላይታ ድቻ

👉”አሁንም ጥቃቅን ነገሮችን በአግባቡ መከወን አለመቻላችን ዋጋ እያስከፈለን ነው።” – ረዳት አሰልጣኝ አታኽልቲ በርኸ

👉”የልጆቹ አዕምሮ ላይ ሰርተን በመምጣታችን ወሳኝ ድል አሳክተናል።” – አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ

ወላይታ ድቻ በሁለቱ አጋማሾች በተቆጠሩ ግቦች ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ረዳት አሰልጣኝ አታኽልቲ በርኸ – ወልዋሎ ዓ/ዩ

“በጨዋታው አቅማችን የፈቀደውን ነገር ለማድረግ ሞክረናል ፤ ነገርግን አሁንም ጥቃቅን ነገሮችን በአግባቡ መከወን አለመቻላችን ዋጋ እያስከፈለን ነው።”

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ

“እጅግ በጣም ጥሩ ጨዋታ ነበር ፤ በነበሩት ሦስት ቀናት የልጆቹ አዕምሮ ላይ ሰርተን በመምጣታችን ወሳኝ ድል አሳክተናል።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link