”መጫወታችን ለፍሬ ካልሆነ አደጋ ነው” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ
”ሶስት ነጥብ ነው ወድ የሆነብን ” አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ
መቐለ 70 እንደርታ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በቤንጃሚን ኮቴ ብቸኛ ግብ በማሸነፍ ወሳኝ ድል ከተቀዳጁበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
” ጨዋታው ጥሩ ነው ምንም ጥቅም የለውም ካላሸንፍክበት እና ዝምብሎ ቀላል ኳሶች እየገቡብህ ከተሸነፍክ በጣም ከባድ ነው። መጫወታችን ለውጤት መጫወታችን ለፍሬ ካልሆነ አደጋ ነው።”
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ
”በፈለግነው ሰዓት ባናገባም ከእረፍት በፊት ጎል ማግባት መቻላችን በዚህ ጌም ደጋግመህ እንደሚታየው አንድ ጎል ከገባ ከሜዳው አኳያ ይዘህ መውጣት ነጥቡ በጣም አድቫንቴጅ ስላለው ያንን ነገር አድርገናል። ሰከንድ ሀፍ ማህብራት ሀይሎች ጫና ለመፍጠር ሞክረዋል ሆኖም ግን በዚህ ጌም ሶስት ነጥብ ነው ወድ የሆነብንና ያንን ነገር ማድረግ ስለቻልን እንደ ስትራቴጂያችን ምንፈልገውን ነገር ይዘን ወጥተናል።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link