የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 1-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሀዲያ ሆሳዕና የአምናውን የሊግ ሻምፒየን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመርታት ነጥቡን 26 ካደረሰበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና

“ከጠንካራ ተጋጣሚ ጋር የተደረገ ጠንካራ ጨዋታ ነበር ፤ አንድ ለባዶ መምራት ከፍተኛ ጫና አለው ያንን ተቋቁመን ተጨማሪ ለማስቆጠር እንሞክራለን ካልተሳካ ያለንን አስጠብቀን እንወጣለን።”

አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

“ጨዋታው እንደተጠባቂነቱ አልነበረም ፤ ቶሎ ቶሎ ሙከራዎች የታዩበት ሳይሆን ይበልጥ ጥንቃቄ የበዛበት ጨዋታ ነበር።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link