ኢትዮጵያ መድን አራተኛ ተከታታይ ድሉን ካሳካበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ደግዓረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ
“ጠንካራ ጨዋታ ነበር ፤ ልጆቻችን የቻሉትን አድርገዋል ነገርግን በትኩረት ማጣት ግብ አስተናግደናል።እግር ኳስ ሂደት ነው ፤ አሁንም እንግዲህ ከፊታችን ያለው ጨዋታ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን።”
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን
“ጠንካራ ስብስብ ያለው እና በሰንጠረዡ አጠገባችን ያለ ቡድን እንደመሆኑ በጥንቃቄ ተጫውተናል ፤ ውጤቱም ጥሩ ነው።ተጫዋቾቻችን በስነልቦና ረገድ የተሻለ ደረጃ ላይ መገኘታቸው አግዞናል።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link