“በሁሉም እግርኳሳዊ መመዘኛዎች የበላይነት ወስደናል።” አሰልጣኝ በረከት ደሙ
“ውጤት በማስጠበቁ ረገድ የልምድ ማነስ ችግር አለ።” አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ
አርባምንጭ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ወላይታ ድቻን 2ለ1 በማሸነፍ ሦስተኛ ተከታታይ ድል ካሳካበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኝ ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ በረከት ደሙ – አርባምንጭ ከተማ
“በሁለቱም አጋማሾች በሁሉም እግርኳሳዊ መመዘኛዎች የበላይነት ወስደናል። የጎል ዕድል በመፍጠሩ በኩል ከሌላው ጊዜ በተለየ ዛሬ ብዙ ፈጥረናል። በዕረፍት ሰዓት ከእንቅስቃሴ አንጻር ብልጫ እንደነበረን ተጫዋቾቼን አሳምኛቸው ነበር።”
አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ
“በየሦስት ቀኑ የተጫዋትነው አራተኛ ጨዋታችን ነው ጫና በዝቶብናል ጨዋታው ተደራራቢ ነው ተጫዋቾቻችን ላይ ድካም ይታይ ነበር። ውጤት በማስጠበቁ ረገድ የልምድ ማነስ ችግር አለብን።
ሙሉውን ለማድመጥ – LINK