የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሾሟል።
ለ12 ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሁም ከሕዳር ወር ጀምሮ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ሲሠሩ የቆዩት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለመምራት ተመርጠዋል።
በተጫዋችነት ዘመናቸው በክለብ ደረጃ ለአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ፣ ወንጂ ስኳር፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አየር ኃይል፣ ጥቁር ዐባይ በመጨረሻም በአርባምንጭ ውስጥ ተጫዋች እና ረዳት አሰልጣኝ በመሆን እግርኳስን እስካቆሙበት ጊዜ ድረስ መጫወት የቻሉት መሳይ በአሰልጣኝነት ዘመናቸው ወላይታ ድቻን ከምስረታው አንስቶ ከታችኛው ዲቪዚዮን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ ትልቅ አስተዋፆ ያደረጉ ሲሆን ከዛ በኋላም በፋሲል ከነማ እና ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲገባ ያስቻለውን አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዳት እና ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ከሠሩ በኋላ በቋሚነት የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።