የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 0-1 ኢትዮጵያ መድን

👉 “ጨዋታውን በምንፈልገው መንገድ ማስኬድ ችለናል ፤ ልዩነቱ ጎሉ ነው።” አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ

👉 “በቡድኔ ደስ ይለኛል ፤ አንድን ቡድን የምትለካለው በመጥፎ ጊዜ እንዴት መወጣት እንዳለበት ሲያውቅ ነው።” አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ

ኢትዮጵያ መድኖች ሀዲያ ሆሳዕናን 1ለ0 በማሸነፍ ተከታታይ 6ኛ ድላቸውን ካሳኩበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።


አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና

“ጨዋታው ከባድ ነው። ያለው ፕሮግራም ለእኛ ጫና አለው። ከ16ኛ ሳምንት ጀምሮ አራት ጨዋታዎችን በ13 ቀናት ነው የምንጫወተው ስለዚህ ድካሞች አሉ። ጨዋታውን በምንፈልገው መንገድ ማስኬድ ችለናል ፤ ልዩነቱ ጎሉ ነው። በይበልጥ ከወገብ በላይ ያሉ ተጫዋቾች ላይ በጣም ድካም አለ።”

አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን

“ተጋጣሚያችን የኃይል አጨዋወት እንደሚጫወቱ ጠብቀን ነበር ፤ ያንኑ ነው ተግባራዊ ያደረጉት። እንደዛም ቢሆን ተቆጣጥረን ለመውጣት ጥረት አድርገን በጥሩ ሰዓት ጎል አግብተናል። በቡድኔ ደስ ይለኛል ፤ አንድን ቡድን የምትለካለው በመጥፎ ጊዜ እንዴት መወጣት እንዳለበት ሲያውቅ ነው። በውድድሩ መጀመሪያ በጉዳት እና ቅጣቶች ምክንያት የነበረውን ፈታኝ ጊዜ በዘዴ ባናልፈው ኖሮ እዚህ ደረጃ ላይ አንደርስም ነበር።

ሙሉውን ለማድመጥ – LINK