የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አስቀድሞ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ባለፈው ሳምንት የሾመው ፌዴሬሽኑ እንዳስታወቀው ብሔራዊ ቡድኑ ከእሁድ ጥር 25 ጀምሮ ለማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት የሚጀምር ሲሆን የካቲት 5 እና 12 ከጅቡቲ ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ያደርጋል። ከአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ በኋላ ሉሊዎቹ በአንደኛ ዙር መርሐ ግብር ከዩጋንዳ ጋር የመጀመርያውን ጨዋታ የካቲት 14 ካምፓላ ላይ እንዲሁም የካቲት 19 አዲስ አበባ ላይ የሚያከናውን ይሆናል።
ብሔራዊ ቡድኑ በ2024 የማጣርያ መርሐ ግብር በቡሩንዲ አቻው በመለያ ምቶች ተሸንፎ ከውድድር መሰናበቱ የሚታወስ ነው።