በዘንድሮው የውድድር ዓመት አዳማ ከተማን የተቀላቀለው ስንታየሁ መንግሥቱ ወደ ሩዋንዳ ያቀና ይሆን?
አዳማ ከተማን በያዝነው ዓመት የተቀላቀለውን አጥቂ ስንታየሁ መንግሥቱን በሩዋንዳ የሚገኘው ክለብ ሊያስፈርመው እንደፈለገ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ፈላጊው ክለብ ኤ.ኤስ ኪጋሊ መሆኑ ታውቋል። ስንታየሁ ከአዳማ ከተማ ጋር ቀሪ ኮንትራት ያለው በመሆኑ ክለቡ ተጫዋቹን እንዲለቅ በወኪሉ ሶከር ኤጀንሲ አማካኝነት ጥያቄ ማቅረቡን እና ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናት ከውሳኔ እንደሚደርስ ሰምተናል።
ኤ.ኤስ. ኪጋሊ እግር ኳስ ክለብ በኪጋሊ ከተማ የሚገኝ የሩዋንዳ እግር ኳስ ክለብ ሲሆን በ1999 የተመሰረተው ቡድኑ በሩዋንዳ ፕሪሚየር ሊግ ይሳተፋል። የሩዋንዳ ዋንጫን ሁለት ጊዜ እና የሩዋንዳ ሱፐር ካፕን ሁለት ጊዜ አሸንፏል። በአሁን ሰዓትም በሊጉ በአራተኛ ደረጃነት ይገኛል።
የእግርኳስ ሕይወቱ በወላይታ ድቻ ጅማሮውን አድርጎ በባህር ዳር ከተማ ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ ዳግም ወደ ወላይታ ድቻ ተመልሶ ከተጫወት በኋላ በሻሸመኔ ከተማ አሁን ለአዳማ ከተማ እየተጫወተ ሲሆን ስንታየሁ በዚህ ዓመት አምስት ጎሎችን በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነትን እየተፎካከረ ይገኛል።