የኢትዮጵያ ዋንጫ በመዲናዋ ከተማ አይካሄድ ይሆንን?

ሦስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ዋንጫ በአዲስ አበባ ሊካሄድ አስቀድሞ መርሐ ግብር ቢወጣለትም በመዲናዋ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

ለአራት ዓመታት ተቋርጦ ባሳለፍነው ዓመት ዳግም ተመልሶ መካሄድ የጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የዘንድሮው ውድድር ሦስተኛ ዙር ላይ መድረሱ ይታወሳል።

በሀዋሳ እና በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ ሊካሄድ የታሰበው ይህ ውድድር በሀዋሳ ከተማ ያሉ ጨዋታዎች አስቀድሞ በወጣላቸው መርሐ ግብር መሰረት እንደሚካሄዱ ሲጠበቅ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄዱ ስድስት ጨዋታዎች ግን የመካሄዳቸው ነገር አጠራጣሪ አድርጎታል።

በመዲናዋ መካሄድ የነበረባቸው ጨዋታዎቹ እንዳይካሄዱ ምክንያት የሆነው በቀጣይ የሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄዱ እንደሆነ ሰምተናል። አወዳዳሪው አካል ውድድሩ በወጣለት ፕሮግራም መሰረት በሌላ ስታዲየም እንዲካሄድ ጥረት እያደረገ ሲሆን ምን አልባት ሰበታ ከተማ ወይ አዳማ ከተማ ላይ ለማድረግ መታሰቡን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።