“ 5 Star Shimeles “

ሽመልስ በቀለ በአንድ ጨዋታ 5 ግቦች ከመረብ አሳረፈ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የጨዋታ አቀጣጣይ ሽመልስ በቀለ ትላንት ምሽት በሱዳን ፕሪሚየር ሊግ ክለቡ አልሜሪክ አልኑስርን 7 1 በረታበት ጨዋታ አምስቱን ሲያስቆጥር ለአንዷ መገኘት አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

የሊቢያውን ታላቅ ክለብ አልኢትሃድ ለቆ በፈረንጆቹ አዲስ አመት መጀመርያ አልሜሪክን የተቀላቀለው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አማካይ በሱዳኑ ክለብ ግብ ሲያስቆጥር የትላንቱ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡

ከጨዋታው በኋላ ለሶካ25ኢስት.ኮም አስተያየቱን የሰጠው ሽመልስ ይህን ያህል ግብ ማስቆጠሩን እንዳልጠበቀው ገልጧል፡፡ ‹‹ ለሆነው ነገር ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ፡፡ በተጫዋችነት ህይወቴ ከዚህ በፊት 5 ግቦች አስቆጥሬ ባለማወቄ ይህንን አልጠበቅኩም፡፡ ነገር ግን ይህ ከሜሪክ ጋር ለማሳልፈው አስደሳች ጊዜያት እንደመንደርደርያ እመለከተዋለሁ ›› ብሏል፡፡

ሜሪክ በሱዳን ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታ ከአል ሂላል ኦምዱርማን ጋር የሚያደርገው የሱዳን ትልቁ ደርቢ በፊት በሰፊ ግብ ማሸነፉ በስነልቦናው በኩል ተጠቃሚ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *