ሀድያ ሆሳዕናዎች አንድ አማካይ ተጫዋች ከከፍተኛ ሊግ ማግኘታቸው ታውቋል።
በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እየተመሩ በዘንድሮው የመጀመርያው ዙር የሊጉ ውድድር ሲጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ በጥሩ አፈፃፀም የጨረሱት ነበሮቹ ከከፍተኛ ሊግ አንድ አማካይ ማስፈረም መቻላቸውን አውቀናል።
ሀድያን የተቀላቀለው ተጫዋቹ ከማል ሀጂ ሲባል የእግርኳስ ህይወቱን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጀምሮ በመቀጠ በመቻል ተስፋ ቡድን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ በተስፋውም በዋናው ቡድን መጫወት ችሏል ፤ በያዝነው ዓመት በሀላባ ከተማ መልካም የሚባሉ ጊዜያትን ያሳለፈው ተጫዋቾቹ በነብሮቹ ጋር አብሮ ለቀናት ልምምድ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።