ብርቱካን ገብረክርስቶስ ነገ በክብር ትሸኛለች

ብርቱካን ገብረክርስቶስ ነገ በክብር ትሸኛለች

ከ20 ዓመት በላይ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በወጥ አቋም ግልጋሎት የሰጠችው ብርቱካን ገብረክርስቶስ ነገ በክብር ልትሸኝ ነው።

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች አንዷ የሆነችው ብርቱካን ገብረክርስቶስ በቅርቡ ራስዋን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሏ ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደምም ብርቱካንን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከዮጋንዳ ጋር በሚኖረው የመልስ ጨዋታ ወቅት በክብር ለመሸኘት በገለፀው መሠረት የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን አውቀናል።

ነገ በሚኖረው የዮጋንዳ ጨዋታ ጅማሮ አስቀድሞ በብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የክብር አቀባበል እንደሚደረግላት እና በፌዴሬሽኑ የተዘጋጀ የዕውቅና ሽልማት መርሐግብር እንደሚኖር ለማወቅ ችለናል።

በሌላ ዜና በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአጥቂነት የረጅም ዓመት አገልግሎት የሰጠችው ረሂማ ዘርጋው በተመሳሳይ ከብሔራዊ ቡድን በክብር እንደምትሸኝ ሰምተናል።