መቐለ 70 እንደርታ ደብዳቤ አስገብቷል

መቐለ 70 እንደርታ ደብዳቤ አስገብቷል

መቐለ 70 እንደርታ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደብዳቤ ልኳል።

ከቀናት በፊት በየአብሥራ ተስፋዬ ጉዳይ ቅጣት የተጣለበት መቐለ 70 እንደርታ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ደብዳቤ አስገብቷል። በውሳኔው ላይ ቅሬታ እንዳለው የገለጸው ክለቡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዲሲፕሊን መመርያ አንቀጽ 98(1) መሰረት ይግባኝ ጠይቋል።

በደብዳቤው በክለቡ፣ በተጫዋቹ እና በአመራሮች የተወሰኑትን ውሳኔዎች እንደማይቀበላቸው የገለጸው መቐለ 70 እንደርታ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጉዳዩን አይቶ እስኪወስን ድረስ ውሳኔው በእግድ እንዲቆይም አያይዞ ጠይቋል።