መቻል ይግባኝ ጠይቋል

መቻል ይግባኝ ጠይቋል

መቻል ስፖርት ክለብ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ደብዳቤ ማስገባቱ ታውቋል።

በያዝነው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በአራት የሊጉ ክለቦች እና በአስራ አምስት ተጫዋቾች ላይ ጥፋት አግኝቻለው በማለት የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ቅጣት ከተላለፈባቸው ክለቦች መካከል መቐለ 70 እንደርታ ቀድሞ የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቱን በትናንትናው ዕለት ገልፀን የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ መቻል ስፖርት ክለብ በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ ማስገባቱን የዝግጅት ክፍላችን አረጋግጧል።

ስፖርት ክለቡ በደብዳቤው ውሳኔውን እንደሚቃወም ገልፆ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጉዳዩን አይቶ እስኪወስን ድረስ ውሳኔው በእግድ እንዲቆይ ጠይቋል።