ያለፉትን 42 ወራት በሲዳማ ቡና ቤት ግልጋሎት የሰጠው መክብብ ደገፉ በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።
በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ይቀርባሉ ተብለው ከተገመቱ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሲዳማ ቡና እንደተጠበቀው ሳይሆን መቅረቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። እስካሁን ከተደረጉት 21 የሊጉ ጨዋታዎች 25 ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዥ 11 ቦታ ላይ የሚገኘው ክለቡ በዛሬው ዕለት ከግብ ዘቡ መክብብ ደገፉ ጋር መለያየቱ ታውቋል።
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ የነበረው መክብብ ከ2014 ጀምሮ በሲዳማ ቡና ቤት ግልጋሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በተለይ ዓምና በርካታ ጨዋታዎች ላይ (የክለቡ 5ኛ ብዙ ደቂቃ የተጫወተ) ሲሳተፍ የነበረው መክብብ ዘንድሮ ብዙም የመሰለፍ ዕድል ሳይገኝ የቆየ ሲሆን ራሱ ተጫዋቹ ጥር 30 ከቡድኑ ጋር ለመለያየት ባቀረበው ይፋዊ ጥያቄ መሰረት ቀሪ የግማሽ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።
