በቼክ ሪፐብሊክ ቆይታ የነበረው ተከላካይ የቡድን አጋሩን ተከትሎ ወደ ቢጫዎች ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
ከቀናት በፊት ሳሙኤል ዮሐንስ ፣ ሀብታሙ ንጉሤ እና ፉዓድ አዚዝ ባዮን ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ላለፉት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመሥራት ላይ የቆየው ሙሳ ራማታን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
በሀገሩ ክለብ ‘kcca’ የእግርኳስ ሕይወቱን ጀምሮ በቼክ ሪፐብሊኩ ‘ኤም ኤፍ ኬ ቪስኮቭ’ እና በአሜሪው ‘Cincinnati 2’ የተጫወተው ይህ የመሃል ተከላካይ በአውሮፓ እና አሜሪካ የነበረውን ቆይታ አጠናቅቆ የቡድን አጋሩ ፉዓድ አዚዝ ባዮን ተከትሎ የወልዋሎ ተጫዋች ለመሆን ከስምምነት ደርሷል።
የዩጋንዳ ከሃያ ዓመት በታች እንዲሁም ዋናውን ብሔራዊ ቡድን ያገለገለው ይህ የሃያ ሦስት ዓመት ተጫዋች በመጀመሪያው ዙር ደካማ ጊዜ ባሳለፈው የቡድኑ የተከላካይ ክፍል በቋሚነት ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል። ከወልዋሎ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ሸገር ከተማ ተጫዋች የሆነው አላዛር ሽመልስ ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።