ሁለገቡ ተጫዋች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆየውን ውል ማራዘሙ ታውቋል።
በዘንድሮ ዓመት የሊጉ ጅማሬ የዓምናውን ጥንካሬያቸውን አጥተው የኋላ የኋላ መሻሻል ያሳዩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የሁለገብ ተጫዋቻቸውን ተመስገን ተስፋዬን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መድን፣ በሻሸመኔ ከተማ እና ከባለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ የሊጉን ዋንጫ ያሳካ ሲሆን አሰልጣኝ በጸሎት ተጫዋቹን በተለያዩ አማራጭ ቦታዎች ሲያጫውቱት መቆየታቸው ይታወቃል።
ተመስገን ተስፋዬ ከእግርኳሱ በተጓዳኝ በ2010 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ኢንጅነሪንግ መመረቁ ይታወሳል።