ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ለዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ጥሪ ደርሷቸዋል

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ለዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ጥሪ ደርሷቸዋል

ከሁለት ሳምንት በኋላ ደርባን ላይ የሚደረገውን የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲመሩት ተመርጠዋል።

በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ተካፋይ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት ከሳምንት በኋላ የማጣሪያ መርሃግብራቸውን ማከናወን ይጀመራሉ። በምድብ ሦስት ተደልድላ  የምትገኘው እና ከሩዋንዳ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል በተመሳሳይ ሰባት ነጥቦች በጎል አንሳ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ዙምባቡዌ በሁለት ነጥቦች ብቻ የምድቡ የመጨረሻው ደረጃ ከተቀመጠችው ቤኒን ጋር መጋቢት 10 ዕለተ ማክሰኞ የምታከናውነውን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲመሩት መመረጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችላለች።

በያዝነው ዓመት የሀገራት እና ክለቦች ጨዋታዎችን በተደጋጋሚ እየዳኙ የሚገኙት በአምላክ ተሰማ በመሐል ፣ ትግል ግዛው እና ተመስገን ሳሙኤል በረዳት ዳኝነት ሲመሩት ሀይለየሱስ ባዘዘው በአንፃሩ አራተኛ ዳኛ በመሆን ወደ ስፍራው ያመራል።

ጨዋታው ዙምባቡዌ ሜዳዋ በካፍ መታገዱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በሚገኘው ሞሰስ ማቤዳ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።