የጦሩ የግብ ዘብ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት

የጦሩ የግብ ዘብ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት

የመቻል ግብ ጠባቂ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሀገሩን እንዲወክል ጥሪ ተደረገለት።

በ2016 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያን እግርኳስ የተዋወቀው የመቻሉ ግብ ጠባቂ አልዮንዚ ናፊያን በተለያዩ ጊዜያት ሀገሩ ዩጋንዳን እንዲያገለግል ጥሪ ቀርቦለት በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮች ሲጫወት ማሳለፉ ይታወቃል። በምስራቅ አፍሪካ በርካታ ግብ ጠባቂዎችን በማውጣት የምትታወቀው ዩጋንዳም ለ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከፊቷ ላሉባት የሞዛምቢክ እና ጊኒ ጨዋታዎች ስብስቧን ዛሬ አሳውቃለች።

በቤልጂዬማዊው አሠልጣኝ ፖል ፑት የሚመሩት ክሬንስ ለሁለቱ ጨዋታዎች ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ሲያቀርቡ ጎልደን አሮውስ እና ቡል ከሚጫወቱት ሁለት የግብ ዘቦች በተጨማሪ የመቻሉ ግብ ጠባቂ አሊዮንዚ እንዳለ ታውቋል።