በቅርቡ ከሲዳማ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው መክብብ ደገፉ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።
ላለፉት ሦስት ዓመት ከስድስት ወራት የሲዳማ ቡና ቆይታ በኋላ በስምምነት ከክለቡ ጋር የተለያየው ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ የሊጉን መሪ መድን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።
ከግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ጋር የተለያዩት መድኖች መክብብ ደገፉን የእርሱ ምትክ በማድረግ ዛሬ የህክምና ምርመራውን ያጠናቀቀ ሲሆን ነገ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
የግብ ዘቡ ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ከተጫወተ በኋላ በ2014 ወደ ሲዳማ ቡና አቅንቶ ላለፉት ሦስት ዓመት ተኩል ጊዜያት ግልጋሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።