የወቅቱ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ተከላካይ ለማስፈረም መቃረቡ ታውቋል።
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እየተመሩ ሊጉን በሰላሳ ስምንት ነጥቦች እየመሩ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድኖች የኋላ ክፍላቸውን ለማጠናከር በማሰብ ተከላካዩ ታዬ ጋሻውን ለማስፈረም መቃረባቸውን ሰምተናል።
የስብስብ ጥልቅት ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያ መድኖች በቅርቡ ከወልዋሎ ጋር በስምምነት የተለያየውን ታዬ ጋሻውን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ተቃርበዋል ፤ በቀጣይ ቀናት የህክምና ምርመራውን በመጨረስ ፊርማውን ያኖራል ተብሎም ይጠበቃል። ታዬ ጋሻው ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ ፣ በአርሲ ነገሌ በቅርቡ ደግሞ በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወቃል።