የመስመር አጥቂው ሐቢብ ከማል ከኢትዮጵያ መድን ጋር ተለያይቶ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ከኢትዮጵያ መድን ጋር ቆይታ አድርጎ የነበረው የመስመር አጥቂው ሀቢብ ከማል ከክለቡ ጋር የሚያቆየው ኮንትራት ቢኖርም ከሰሞኑ በስምምነት መለያየቱን ተከትሎ ወደ ምስራቁ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
ሀቢብ ከማል ድሬዳዋ ከተማን ለመቀላቀል ትላንት የህክምና ምርመራውን ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በይፋ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል ።
ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ በኮልፌ ቀራንዮ እንዲሁም አርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን መጫወት የቻለው ሐቢብ በቀጣይ ቀናት ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሚያደርገው ዝውውር ያገባድዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ ዜና ድሬደዋ ከተማ ከመስመር አጥቂያቸው ተመስገን ደረሰ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።