የትናንሾቹ ሉሲዎች አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ከወሳኙ ጨዋታ በፊት ምን አሉ?

የትናንሾቹ ሉሲዎች አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ከወሳኙ ጨዋታ በፊት ምን አሉ?

👉 “ተጋጣሚያችን ለፍቶ ያስቆጠረብን አንድ ጎል ነው ፤ አራቱን እኛ ነን የሰጠናቸው።”

👉 “ጨዋታው ሲጀምር ባልሠራንበት መንገድ ጎል አግኝተናል ከ15 ደቂቃ በኋላ ግን በእኔ ቁጥጥር ሥር አልነበረም”

👉 “እዚህ ሠርተን በሄድንበት ነው ጎል የተቆጠረብን”

👉 “ያለን ሀሳብ የነበረንን ስህተት ቀንሰን ውጤቱን ለመቀልበስ ነው”

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከካሜሮን ጋር የተደለደለ ሲሆን ካሜሮን ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታም 5ለ2 ተሸንፎ ተመልሷል። ሆኖም ነገ በአ.አ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከሚደረገው የመልስ ጨዋታ በፊት የሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች አሰልጣኞች ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በቅድሚያም የአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊን ሀሳብ እናጋራችሁ…

“ካሜሮን ላይ ሠርተን በነበረበት መንገድ ነው ከቆሙ ኳሶች ጎሎች የተገኙብን አጠቃላይ ግን ከሜዳ ውጪ ጎሎችን ማስቆጠራችን ተጫዋቾቻችን ላይ ተነሳሽነት ፈጥሯል። ያለን ሀሳብ የነበረንን ስህተት ቀንሰን ውጤቱን ለመቀልበስ ነው። አብዛኞቹ ተጫዋቾች አዲስ ናቸው ፤ ሰዓቱንም ብናይ በምሽት በባውዛ መጫወታቸው ትንሽ ግራ አጋብቷቸው ነበር። ቀድመን ካገባን በኋላ መረጋጋት አልቻሉም። ለራሳቸው ከፍተኛ ግምት ነበር የሰጡት ከተጋጣሚ አንጻር እና ቀድመን ስናስቆጥር ከፍላጎታቸው የተነሳ መረጋጋት ይጎድላቸው ነበር። ላረጋጋቸው ሞክሬ ነበር ግን ስሜታቸው ከፍ ያለ ስለነበር እኔንም እያዳመጡኝ አልነበረም። ልምድ ቢኖራቸው ኖሮ በታይም ማኔጂመንት ሦስት ነጥብ ይዘው ይወጡ ነበር። የተጋጣሚያችን ዕድሜ ነገር ካፍ የሚያየው ነው ያው ሪፖርቴ ላይ ማቅረቤ አይቀርም በትክክለኛ ዕድሜ ላይ ነበሩ ብዬ አላስብም። ጨዋታው ሲጀምር ባልሠራንበት መንገድ ጎል አግኝተናል ከ15 ደቂቃ በኋላ ግን በእኔ ቁጥጥር ሥር አልነበረም። ተጋጣሚያችን ለፍቶ ያስቆጠረብን አንድ ጎል ነው አራቱን እኛ ነን የሰጠናቸው። በነገው ጨዋታ የኢትዮጵያ እግርኳስ ወዳድ ሕዝብ መጥቶ እንዲደግፈን እጠይቃለሁ።