የታገዱ ክለቦች እነማን ናቸው?

የታገዱ ክለቦች እነማን ናቸው?

አምስት ክለቦች ዝውውር እንዳይፈጽሙ ታግደዋል።

አምስት ክለቦች በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዝውውር እንዳይፈጽሙ ዕግድ ተጥሎባቸዋል።

በ2016 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ “በስቴዲየሙ የመሰረተ ልማት ውድመት አድርሰዋል” የተባሉት ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ የተበየነባቸውን የካሳ ክፍያ ባለማጠናቀቃቸው ዝውውር እንዳይፈጽሙ ዕግድ የተጣለባቸው ሲሆን ስሑል ሽረ ደግሞ የጋናዊውን አጥቂ ቢስማርክ አፖንግ ውዝፍ ደመወዝ ባለመክፋሉ በፊፋ ተከስሶ ዕግድ የተጣለበት ሌላኛው ክለብ ሆኗል።

አራተኛው የታገደው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ ሲሆን የቀድሞ ተጫዋቹ ቢያድግልኝ ኤልያስን ደመወዝ ባለመክፈሉ የታገደ ክለብ ነው። አዳማ ከተማም የአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን ውዝፍ ደመወዝ ባለመክፈሉ ዝውውር እንዳያከናውን ዕግድ ተጥሎበታል።