ዛሬ ሌሊት ወደ ሞሮኮ ከሚያቀናው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች ተቀንሶ 23 ተጫዋቾች እንደሚጓዙ እርግጥ ሆኗል።
ለ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ እና ከጂቡቲ ጋር ላለበት ጨዋታ ልምምዱን ሲሰራ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቶ አጠናቋል። ዕኩለ ሌሊት ላይ ወደ ሞሮኮ የሚያቀናው ብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ካደረገላቸው 24 ተጫዋቾች መካከል አንድ ተጫዋች ሊቀነስ እንደሚችል አስቀድመን መረጃ አድርሰናቹሁ ነበር። በዚህ መነሻነት ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መሠረት የተቀነሰው ተጫዋች የግራ መስመር ተከላካይ አብዱልሰላም የሱፍ መሆኑ አውቃለች።
በዚህም መሠረት ወደ ሞሮኮ የሚያቀኑት ሃያ ሦስት ተጫዋቾች
ግብ ጠባቂዎች – ሰዒድ ሀብታሙ፣ አቡበከር ኑራ እና ቢኒያም ገነቱ
ተከላካዮች – ብርሃኑ በቀለ፣ ራምኬል ጀምስ፣ አሥራት ቱንጆ፣ አማኑኤል ተርፋ – አሕመድ ረሺድ፣ ኧፍሬዘር ካሳ፣ ያሬድ ካሳዬ፣ ወልደአማኑኤል ጌቱ እና አስቻለው ታመነ
አማካዮች – አማኑኤል ዮሐንስ፣ ወገኔ ገዛኸኝ፣ በረከት ወልዴ፣ ብሩክ ማርቆስ፣ አብዱልከሪም ወርቁ እና ሀብታሙ ተከስተ
አጥቂዎች – አቡበከር ናስር፣ አሕመድ ሁሴን፣ ቸርነት ጉግሳ፣ መሐመድ አበራ፣ በረከት ደስታ ናቸው። ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ሌሊት አስር ሰዓት ወደ ሞሮኮ የሚያቀና ይሆናል።