የዋልያውን እና የፈረኦኑን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

የዋልያውን እና የፈረኦኑን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

የፊታችን ዓርብ እኩለ ለሊት የሚደረገውን የኢትዮጵያ እና ግብፅ ፍልሚያ የሚመሩ አልቢትሮች ተለይተዋል።

ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ 4ኛ እና 5ኛ ጨዋታዎች ካለንበት ሳምንት አንስቶ መደረግ የሚጀምሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ሞሮኮ ላይ ለሚደረጉት የግብፅ እና ጂቡቲ ጨዋታዎች ካሳለፍነው ሳምንት አንስቶ ዝግጅቱን ጀምሯል። ዓርብ እኩለ ለሊት 6 ሰዓት ዛውሊ ስታዲየም የሚደረገውን ፍልሚያም የሞሪሺየስ እና የሲሼልስ አልቢትሮች እንደሚመሩት ታውቋል።

የሞሪሺየስ ዜግነት ያላቸው ፓትሪስ ሚላዛሬ በዋና ዳኝነት እንዲሁም የሀገራቸው ልጅ የሆኑት ፋቢን ካውቬሌት እና ከሲሼልስ ሀገር የመጡት ሻጂ ፓዳያቺ በረዳትነት በተጨማሪም እንደ ሻጂ ከሲሼልስ የሆኑት ኬረን ዮሲቲ አራተኛ ዳኛ ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸው ታውቋል።